የስም ትርጉም !! አናሲሞስ ማለት የግሪክ አመጣጥ ያለው የወንድ ስም ሲሆን ትርጉሙም ‹የሚረዳ ፣ ጠቃሚ ፣ ፍሬያማ› ማለት ነው።
ህፃናት...
ህጻናት ስንል ማየት የሌለባቸውን ነገሮች በጎዳና ሕይወት ውስጥ እያዩ በልመና ስራ ውስጥ ተሰማርተው ብርድ ረሃብ አና ጥም እየተጫወተባቸው በለጋ እድምያቸው በሱስ ውስጥ ብርድ እና ረሃብን ከራሳቸው ለማስቀረት ሲሉ ማስቲሽ በመሳብ በሳምባቸው ለይ ጉዳት እንደሚያመጣ ሳይረዱ እድሜያቸውን በአጭር ለምቀጩ ህጻናት እንዲሁም መማር ፈልገው የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት ለከበዳቸው ህፃናት ምን እናድርግ ? ስንል አሰብን
ሴቶች..
ሴቶች ስንል ደሞ በጎዳና ሕይወት ውስጥ ልክ አንደ ህጻናቶቹ እጣ ፋንታ ሆኖባቸው የምኖሩ ስሆኑ ጉዳታቸው በጎዳና ሕይወት ውስጥ ሲኖሩ ጾታዊ ጥቃት... አስገድዶ መድፈር፣የወስብ ንግድ ፣ ፆታዊ ትንኮሳ ፣ ግብረ-ሰዶምና እየደረሰባቸው ለምኖሩ እህቶቻችን ምን እናድርግላቸው? አልን
በዚ በኩል ደሞ
ወጣቶች...
ወጣቶች ሆኖም ግን፣ በተለያዩ ምክንያቶች ከወላጆቻቸው፣ ከቤተሰቦቻቸው፣ ከማኅበረሰባቸው ተለይተውና ርቀው በጎዳና ሰቅጣጭ ህይወት ውስጥ ገብተዋል ስለዚህ፣ በእግርዎ ሲጓዙም ሆነ፣ በመኪና ሲንቀሳቀሱ ከፊት-ከኋላ፣ ከግራ-ቀኝ እጅዎትን ይዘው አሊያም ደግሞ የመኪናዎትን መስኮት ቆርቁረው የሚማጸኑትን ወጣቶች በተለያዩ ሱስ አስያዥ ንጥረ ነገሮች እየደነዘዙ የጎዳና ልጆች ሰቅጣጭ ህይወት እያዩ ማለፍ እጅግ አሳዛኝ መሆኑን የተመለከተ ሁሉ ያውቀዋል፡፡እንዲህ ዓይነት የጎዳና ህይወት የቀን ተቀን ትርዒት፣ ከናዝሬት/አዳማ ከተማ ባሻገር ባሉ ዋና ዋና ከተሞች አንደ አዲስ አበባ ፣ሀዋሳ፣ ሻሸመኔ፣ ባህር ዳር፣ ደብረ ብርሃን፣ ድሬዳዋ እና ሌሎች ከተሞች በየጎዳናው ላይ ዘወትር ይታያሉ። ‹‹የጎዳና ልጆች!›› የሚል ሥያሜ ማኅበረሰቡ የሰጣቸው ስም ነው እንጂ እነርሱ ግን ቀረብ ብሎ የማናቹ ብሎ ላናገራቸው ሰው ሁሉ የእከሌ እና የእከሊት ልጅ ነኝ ነው የሚሉት፡፡
ቆይ ወጣቶቹ በጎዳና ጸሐይ እና ሀሩር ጥቁርቁር ብሏል፤ ጸጉራቸው ካለመታጠብና ከቅባት እጥረት የተነሳ እርስ በእርሱ ተፈታትሎና ተያይዞ በተባይ ቀጭመዋል፤ ከንፈራቸው በሲጋራ ጭስ በልዞ- ደርቋል፤ አንገታቸው በጭቅቅት ጠቁሯል ፣ ለግላጋ ታዳጊ ቁመታቸው ከከሰመና ሰውነታቸው ከመክሳታቸው ጋር ተደምሮ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዳለባቸው ያሳብቅባቸዋል ፤ የለበሱት ልብስ የተቦጫጨቀና የቆሸሸ ቲሸርቱ ያለቀ ጂንስ ሱሪ (ስለሰፋቸው በቀበቶ ፈንታ በገመድ አስሮውታል) ባለመታጠባቸው በቆሻሻ ደርደዋል፤ በእግራቸው ሁለት የተለያየ ነጠላ ጫማ ቢጫሙም፣ ተረከዛቸው መሰነጣጠቁ ጎልቶ ይታያል፤ በዚህ ላይ ጫፉ በተቆረጠ የውሃ ሀይላንድ ላስቲክ ውስጥ ይዞ የሚስቡት ‹‹ማስቲሽ›› የአካባቢውን አየር ይበክላል፤ ይህ ሁሉ ተዳምሮ አጠገባቸው ቆሞ ለሚያናግራቸው ሰው ከሰውነታቸው እና ከለበሱት ልብሳቸው ከሚወጣው ጠረን ጋር ተቀላቅሎ ለአፍንጫ ስለሚሸት ወደዱም ጠሉም ያስነጥሶታል፡፡ እጅግ መራር ያለ ተደጋጋሚ ማስነጠስም፤ አንጢሹ! ሆኖም ሌላም ነገር ብሉዋቸው ይህ ለእነርሱ ምናቸውም አይደለም፤ የዘወትር ኑሮዋቸው እና ህይወታቸው ስለሆነ ፡፡
እንዲሁም አረጋውያን
አረጋውያን ሰብአዊ ክብራቸው ተጠብቆና በቂ የኑሮ ደረጃ፣ የተሟላ የጤና አገልግሎት የማግኘት፣ እንዲሁም በተለያዩ ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የመሳተፍ መብቶች ያላቸው ቢሆንም፤ በተግባር ግን በርካታ ተግዳሮቶች ይገጥሟቸዋል፡፡ መሰረታዊ ፍላጎታቸው ያልተሟላላቸው፣ በተለያዩ የጤና ችግሮች የሚሰቃዩ፣ ገቢ የሌላቸው እና በማኅበራዊ ዋስትና (ኢንሹራንስ) አገልግሎት እጦት በየጎዳናው የወደቁ አረጋውያን አሉ፡፡
በአጠቃላይ
ታድያ ይሄንን አይተን የማለፍ አቅሙን ስናአጣ እኛ አናሲሞሶች ምን እናድርግ ስንል አንድ ሃሳብ አሰብን ብዙ ጊዜ ሰዎች ስለ ወጣቶች የምሉት ነገር ትዝ አለን እንዲህ ይላሉ ወጣትነት ሃይል ነው ፤ምንም ሳይኖረው በተስፋ እና በራዕይ የተሞላ ነው ። ወጣትነት ድፍረትን ይጠይቃል ፤ እችላለሁ በሚል መንፈስ መጎልመስ አለበት ይሉናል ።
ስለዚህ እኛ አናሲሞሶች በተመሳሳይ ሀሳብ አና በሙሉ ፍላጎት በውስጣችን በተነሳሳው ሀሳብ በመነሳት ህጻናት ፣ሴቶች እና ወጣቶች አንዲሁም አቅመ ደካማ አረጋዊያን አና አካል ጉዳተኞችን በጎዳናዎች ለይ የምኖሩትን በማንሳት እና በስነልቦና አስተማሪ አስተምረን የተሻለ ሕይወት እንድኖሩ የሚል ራዕይ ይዘን አናሲሞስ የበጎ አድራጎት ድርጅት የሚባል ድርጅት መስርተናል።
ህጻናት ሴቶች እና ወጣቶች ካለባቸው የጎዳና ኑሮ እና ሱስ አንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ፣ መሃበራዊ ፣ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ችግር እና ጉስቁልና ተላቀው ብቁና እና የሰለጠኑ ሃላፊነትን የሚሸከሙ በስነምግባር የታነጹ የነገይቷን ኢትዮጵያን የሚረከቡና ሚገነቡ ዜጎች ሆነው ማየት ነው ።
ህጻናት ሴቶች እና ወጣቶችን ማስተማር እና እንዲሁም አቅም ያጡ አረጋውያን ካለባቸው የጎዳና ኑሮ እና ሱስ አንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ችግር , መሃበራዊ ተግዳሮት፣አካላዊ ጉስቁልናና ከስነልቦናዊ ችግር ተላቀው ብቁና እና የሰለጠኑ ሃላፊነትን የሚሸከሙ በስነምግባር የታነጹ የነገይቷን ኢትዮጵያን የሚረከቡና ሚገነቡ ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ ነው ።
Description Lorem ipsum, dolor sit amet consectetur adipisicing elit. Facilis, dolore.
Description Lorem ipsum, dolor sit amet consectetur adipisicing elit. Facilis, dolore.
Description Lorem ipsum, dolor sit amet consectetur adipisicing elit. Facilis, dolore.
Description Lorem ipsum, dolor sit amet consectetur adipisicing elit. Facilis, dolore.
Description Lorem ipsum, dolor sit amet consectetur adipisicing elit. Facilis, dolore.
Description Lorem ipsum, dolor sit amet consectetur adipisicing elit. Facilis, dolore.
Address: መብራት ሃይል አዋሽ ባንክ ፊት ለፊት እምሩ ህንጻ ቢሮ ቁጥር 125
Phone: +251 96 202 1758
Phone: +251 94 106 5544
Email: info@Anasimos.com